Article

የምርጫ ወቅት የትምህርት መርሃ ግብርን ይመለከታል

6ኛውን ሀገራዊ ምርጫ ላይ ተማሪዎች ለመሳተፍ ይችሉ ዘንድ ከምርጫ ቦርድና ከሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር በተሰጠ አቅጣጫ መሰረት የሴሚስተር እረፍት ጊዜን እና መደበኛ የገጽ ለገጽ መማር ማስተማር ሂደት ለጊዜው ከታች በተቀመጡት አቅጣጫዎች መሰረት የሚከናወኑ ይሆናል፡፡
1. የቅድመ ምረቃ ፕሮግራም የ1ኛ ሴሚስተር ፈተና ከግንቦት 30 ቀን 2013 እስከ ሰኔ 8 ቀን 2013 ዓ.ም ይሰጣል፡፡
2. የቅድመ ምረቃ ተማሪዎች በሙሉ – ከምርጫው በፊት አንድ ሳምንት ማለትም ከሰኔ 9 እስከ 13 እና ከምርጫው በኋላ አንድ ሳምንት ከሰኔ 14 እስከ 20 ዓ.ም ድረስ ብቻ የሴሚስተር እረፍት ሲሆን ከሰኔ 9 ቀን እስከ 20 ቀን 2013 ዓ.ም ትምህርት የማይኖር ሲሆን በዚሁ ጊዜ ተማሪዎች ወደመጡባቸው አካባቢዎች በመሄድ ምርጫ ላይ ይሳተፋሉ
3. ትምህርት ዝግ በሆኑበት ቀናት በዩኒቨርስቲው ግቢ ውስጥ መቆየት የሚፈልጉ መደበኛ ተማሪዎች የዩኒቨርስቲውን ህግና ደንቦችን በማክበር መቆየት የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
4. የተከታታይ (Extenstion) ተማሪዎች ከምርጫው በኋላ በሚኖረው አንድ ሳምንት ማለትም ከሰኔ 14, 2013 እስከ ሰኔ 20, 2013 ዓ.ም ብቻ የመማር ማስተማር ሂደት አይኖርም፡፡
5. ሁሉም የድህረ ምረቃ ተማሪዎች በሙሉ ከምርጫው በኋላ አንድ ሳምንት ማለትም ከሰኔ 14 እስከ 20 2013 ዓ.ም ድረስ ብቻ ትምህርት በኦንላይን (Virtual) አማራጭ ይካሄዳል፡
6. የአዲስ ገቢ የአንደኛ አመት ተማሪዎች ኦንላይን ምዝገባ በሰኔ 1-2 ቀን 2013 ይካሄዳል፡ከሰኔ 19-20 ቀን 2013 ዓ.ም ወደ ዩኒርሲቲው በመምጣት ሪፖርት ያደርጋሉ፡፡ የገጽ ለገጽ ትምህርት የሚጀመረው ሰኔ 21 ቀን 2013 ዓ.ም ይሆናል፡፡

ሁሉም ኮሌጅ ዲኖች፤ ዳይሬክተሮች፤ተማሪዎችና የዩኒርሲቲው ህብረተሰብ በሙሉ ከላይ በተጠቀሰው መሰረት አስፈላጊውን ዝግጅትና ክትትል በማድረግ እንዲፈጽሙ እናሳውቃለን፡፡
አዲስ አባባ ዪኒቨርስቲ ሬጅስትራር